Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ብድር ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 መሠረት ተረክቦ ሁለት ጊዜ ሐራጅ ወጥቶ ሳይሸጥ የቀረውንና ባንኩ በቋሚነት የተረከበውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ብድር ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው የመያዣ  ሰጪው/ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሚሸጠው ንብረት አይነት

የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ

ቀሪ የመሬት ሊዝ ውል (በዓመት)

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)

የሐራጁ ደረጃ

 

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት

1

ተድላ አብረሃ እርሻ ልማት

በጋምቤላ ///መንግሥት ኢታንግ ልዩ ወረዳ ዋንኬ ቀበሌ

የእርሻ መሬት

 

50 ሄክታር መሬት ላይ የተቋቋመና 474.60 ሄክታር የለማ የእርሻ መሬት ያለው

35

 

22,139,653.67

 

ዝግ ጨረታ

 

ጋምቤላ ዲስትሪክት /ቤት፣ መስከረም 11 ቀን 2019 . ከጠዋቱ 400 እስክ 600 ሠዓት

የሕንፃ ግንባታዎች

ሁለት የሠራተኛ የመኖሪያ፣ ቢሮ፣ ሁለት መጋዘን፣ ጋራጅ እና የጥበቃ ቤት ያለው

የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች

 

1. አንድ DEUTZ FAHR ትራክተር 70HP 2011 ስሪት

2, ሁለት ባለ 24 አንድ ዲስክ መከስከሻ

3, አንድ ባለ 4 ዲስክ ማረሻ

4. ሁለት መዝሪያ /Planter

5. አንድ ኬሚካል መርጫ

ተከርካሪዎች

1. ባለ ሁለት ጋቢና ትዮታ ፒካፕ ተሸከርካሪ 2014 ስሪት

2, አንድ የደረቅ ጭነት አይሱዚ/SUZU FSR/ተሸከርካሪ

የጨረታው መመሪያ፦

1. ተወዳዳሪዎች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ዓላማ በባንኩ ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 10:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።

2.ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ / CPO) ብቻ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።

3.አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ አለበት። ይህ ካልሆነ ግን ያስያዘው CPO ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሠንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በጋምቤላ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤት ይካሄዳል። ሕጋዊ ሰውነት ያላቸውን አካላት ወክለው የሚቀርቡ ሰዎች የሥራች ጽሑፍ፣ የንግድ ምዝገባ፤ የንግድ ፈቃድ አና የተረጋገጠ ውክልና ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ሕጋዊ ክፍያዎችን (ካለ) ገዢው ይከፍላል።

6. አንዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች (ለምሳሌ ትራከተሩ) ከቀረጥ ነፃ የገቡ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ገዢው ተመሳሳይ የቀረጥ ነፃ መብት ያለው ወይም የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል የሚስማማ መሆን አለበት።

7. የጨረታው አሸናፊ የባንኩን የብድር መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ባንኩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከፊል ብድር (ዱቤ ሽያጭ) ሊመቻችለት ይችላል።

8. የንብረቱ ስም ወደ ገዢው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፤ ገዢው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈጽማል።

9. ተጫራቾች ንብረቱን መጎብኘት የሚችሉት ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር አስቀድመው ቀጠሮ በመያዝ ይሆናል።

10. ለተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251475512577 / +251475512588 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-21 10:00
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T10:02:30.000Z
← Back to all tenders