Other Sales
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተለያዩ እቃዎች እና ተሽከርካሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 05/2019 ዓ.ም
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ dorco/ ምላጭ አልባሳት፤ኮስሞቲክስ፣ አጎበር USB CABLE እና Hik Vision Network Camera በግልፅ እንድሁም ጫማ ፣ወንበር /office chair/፣ አልባሳት እና ተሽከርካሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-
1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የዘመነን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሸከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ-18-አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
2) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
3) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርትፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገዉም፡፡
4) በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
5) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
6) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
7) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታዉ 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡
8) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡በተሰጠው የጊዜገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ግቢ ተደርጎ እቃዉ እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡
9) ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡
10) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
11) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 ሁለት መቶ ሺህ ብር እንድሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
12) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 033 551 0693 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kombolcha Custom Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T11:32:24.000Z