Transportation Service
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኦክስጂን ሙሌት እና የትራንስፖርት ጭነት ማመላለሻ መኪና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ -ማ/ቁ 01
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ 01/2018 ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የኦክስጂን ሙሌት እና የትራንስፖርት ጭነት ማመላለሻ መኪና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳታፍ የሚፈልጉ ተጫረቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ኦርጅናል እና ኮፒ የመንግስት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት/TIN number/ኦርጅናልና ኮፒ በተለይየ ፖስታ ካሸጉ በኃላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. እያንዳንዳቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልፅ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን /VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት።ካልሆና እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
4. የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 57 በአካል በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታው ዶክመንት በታሸጋ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የጫረቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋት በ4፡00 ሰዓት የጨራታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥን ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
6. አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎችን የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ እንዲሁም የትራንስፖርት በረሱ ወጪ የሚያቀርብ ይሆናል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጀ፡- በስልክ ቁጥር 046 556 0281 / 09 26 18 21 11 / 09 41 98 51 65 ላይ መደወል ይቻለል።
አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋት በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-05 15:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በ9፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Halaba Kilito General Hospital
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T12:00:03.000Z