Spare Parts and Car Decoration Materials
በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01 /2019
በአማራ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ -
- ሎት 1 የመኪና እቃ መለዋወጫዎች አመታዊ ኮንትራት ግዥ
- ሎት 2 የመኪና ጎማ አመታዊ ኮንትራት ግዥ
- ሎት 3 የመስተንግዶ አገልግሎት አመታዊ ኮንትራት ግዥ
- ሎት 4 የጭነት አገልግሎት አመታዊ ኮንትራት ግዥ
- ሎት 5 የመኪና ዘይት እና ቅባት አመታዊ ኮንትራት ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TT ያላቸው
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ለመኪና እቃ 50,000/ሀምሳ ሽህ ብር/ ለሎት 2 ለመኪና ጎማ 30,000/ ሰላሳ ሽህ ብር/ለሎት 3 ለመስተንግዶ 10000/ አስር ሽህ ብር፣ ለሎት 4 ለጭነት 10000/አስር ሽህ ብር/ ለሎት 5 ለመኪና ዘይት እና ቅባት20000/ሀያ ሽህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16 ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ በማስገባት ይታሸጋል።በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በስራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል ፡16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል።
7. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር -033-450-02-22 በመደወል ማግኘት ይቻላል
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጎልም ::
9. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ::
10. ውድድሩ የሚካሄደው ከ ሎት እስከ ሎት 5 በየምድቡ በሎት ነው፡
11. የእቃው ማስረከቢያ ቦታ ሎት 2 መቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በየንብረት ክፍሉ ሲሆን ሎት 1 እና ሎት 5 የመኪና መለዋዎጫ እቃዎች እና የመኪና ዘይትና ቅባት መኪኖች ለጥገና አገልግሎት ጋራጅ በሚገቡበት ጊዜ የጥገና አገልግሎት በሚሰጠው ጋራጅ / ደሴ ከተማ/ በመገኘት በባለሙያና በጋራጅ የተረጋገጠ ኦርጅናል እቃ ለንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል እንድሁም እቃዎች በሚፈለጉበት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት የማቅረብ ግዴታ አለበት።እንድሁም ሎት 3 እና ሎት 4 ተቋማቶች አገልግሎት በሚፈልጉበት ቦታ እና ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት ማቅረብና ማድረስ አለበት።
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመቅደላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South Wollo Zone Mekedela Wereda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T08:48:19.000Z