Machinery and Equipment
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሳር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨራታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፦
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. ለጨረታው የወጣ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት ሞዴል 204 የሆነ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር አአ-05-02431 መነሻ ዋጋ 6,500,000 (ስድስት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር) እንገልፃለን።
2. ሁለት ትሬሸሮች በትራክተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑት የአንዱ መነሻ ዋጋ 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ሲሆን የሁለቱ ዋጋ አንድ ላይ 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺ ብር) መሆኑን እንገልፃለን።
3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአርባጉጉ የገ/ሕስራ/ዩኒየን/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑንና ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ወይም መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል የሆነ የዘመኑ የናሽናል ID (የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ) ማቅረብ እና ድርጅት ከሆነ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለያንዳንዱ ለጨርታውን ለቀረቡት ንብረቶች 10% CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
6. ለጨረታው ለቀረቡትን ንብረቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 10፡00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሮች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ግቢ ውስጥ ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ኤፌሰር የጭነት መኪናውን ማየት ይችላሉ።
7. ለጨረታው የቀረቡትን ሁለት ትሬሸሮች በአርሲ ዞን በጮሌ ወረዳ በአርባ ጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን መጋዘን ያለበት ግቢ ውስጥ በግልፅ ማየት ይችላሉ።
8. ጨረታው በ6ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት ) ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአርባጉጉ የገ/ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ተዘግቶ በ5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
9. ጨረታው በ16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት) ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት በ5፡00 (ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
10. ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ እና የናሽናል ID (የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ) ማቅረብ አለበት።
11. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መውሰድ አለበት።
12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 21 09 68 80/ 09 20 06 31 65/ 09 17 03 43 43 ደውለው መረዳት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
አድራሻችን፦ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01 ቀበሌ መሆናችንን እንገልፃለን።
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-09 11:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 (ሰዓት)
- Region: Oromia
- Publishing entity: Arbagugu Farmers Cooperative Union
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T08:26:15.000Z