Aluminium Products

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፤ የተለያዩ ጎማዎች፤ የተለያዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

 ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

03/2019 ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ፣ የተለያዩ ንብረቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ

  • የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፤
  • የተለያዩ ጎማዎች፤
  •  የተለያዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች እና
  • የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የኤጀንሲው አድራሻ፤ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት ጨፌ አናኒ ሕንፃ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3th Floor) ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግሥትንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd  floor) ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡  የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30–6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
  2. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30–6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 08 ቀን 209 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4.  ጨረታው መስከረም 08/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 10% /አስር ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ CLO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ CPO ለማሠራት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-15-57-70 27

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ገዥና

ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

(ፊንፊኔ)


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-09-18 11:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Public Procurement and Property Disposal Agency
  • Buyer address: Sarbet, Kera road, In front of Pushkin square on Bethlehem Building 3rd floor
  • Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T07:30:09.000Z
← Back to all tenders