Audio Visual, Photography and Filming Service and Equipment
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ዕቃዎችን ለመሸጥ ያወጣውን የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቀን ማስተካከያ አድርጎበታል
More tags
Description
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የማይጠቀምባቸውን የተለያዩ ያላገለገሉ የመኪና መለዋወጫ፣ ያገለገሉ የእንጨት እና የፕላስቲክ በሮች፣ መስኮቶች፣ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በርሜሎች፣ “Auxiliary (Mixer, Compressor, Generator etc.)” የቢሮ ዕቃዎች “computer, Laptop, Printer, scanner etc.” የሆኑትን በግልጽ ጨረታ ቁጥር ኦኮኮ-002/2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ መውጣቱ ይታወቃል።
በመሆኑም የጨረታው መዝጊያ ቀን ከጳጉሜን 3/2018 ዓ.ም ወደ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ስለተራዘመ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ቃሊቲ ከመካኒኮች ማሠልጠኛ ፊት ለፊት ካለው ከኮርፖሬሽኑ ግዥ ክፍል 1ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ከ2፡00 እሰከ 11፡00 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው መስከረም 14/2019 ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተዘግተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ ዕለት 5፡30 ላይ ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6a843e4d0a538a876c000001
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-09-24 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Construction Corporation (OCC)
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T09:06:19.000Z
- Source: 2merkato