Spare Parts and Car Decoration Materials

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ እና የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ እና የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት -

1) የከባድ ተሽከርካሪ መኪና መለዋወጫ ግዥ -ሎት ምድብ 01/2019

2) የጋራዥ አላቂ ዕቃዎች-ሎት ምድብ 02/2019

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።

1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፣

6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር: 046-212-1334

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-07 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T08:57:32.000Z
← Back to all tenders