Textile, Garments and Uniforms
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Sidama
More tags
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServicePersonal Care Products and ServicesFood and BeverageFood Items and DrinksSpare Parts and Car Decoration MaterialsOther SalesSales, Disposals and ForeclosureTelecommunication EquipmentHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingHouse FurnitureOffice FurnitureTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseAmharic2merkatoHawassa Custom Commission Branch Bureau
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ማስታወቂያ ቁጥር- 07/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት
- የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች ፣
- አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣
- የኤሌክትሪክ/
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
- የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች
- የቤትና ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
- የተለያዩ የምግብ ነከ ዕቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሽጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡oo ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሃሳቦችና ቀረጥ ተመላሽ አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት https://t.me/hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሃደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የጨረታ ዋስትና (CPO) መጠን ለእያንዳንዱ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ የሀራጅ ጨረታ ተሳታፊዎች ምዝገባ ተጀምሮ እንደተጠናቀቀ ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለዉ ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አልያም አይነበብልኝ ማለት አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በዉስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳትይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046-212-53-96/046-212-65-95
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa Custom Commission Branch Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T08:02:21.000Z