Equipment and Accessories

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይከሎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-05/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ፣ ሸቀጣሸቀጥ ልዩ ልዩ እቃዎች)፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ የተሽከርካሪ ጐማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይከሎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. በጨረታው የወጡትን ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም እድሜው ከ8 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟላ በቀበሌ መታወቂያ ብቻ መጫረት ይችላል።

.

 

የእቃው አይነት

 

ጨረታው አይነት

 

በአዲስ ዘመን

የታተመበትት ቀን

 

ጨረታው

የሚካሄድበት ቀን

 

የጨረታው

የሚጀመርበት ሰዓት

 

 

ጨረታው

የሚከፈትበት

ሰዓት

 

ስልክ ቁጥር

 

1

ኤሌክትሮኒክስ

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

 

 

 

 

 

09221118429/0222118925

 

2

ኮስሞቲክስ

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

3

የተሸከርካሪ መለወዋጫዎች

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

4

ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ ዕቃዎች)

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

5

የኮንስትራክሽን

ማቴሪያል

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

6

የተሸከርካሪ ጎማዎች

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

7

የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

8

ያገለገሉ ሞተርሳይክሎች

 

ግልፅ

25/12/2018

02/13/2018

4:00

8:00

የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቀዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

5. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Commission Adama Branch Office) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

 7. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10.ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11.ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

12.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13.ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

N.B: በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉም ጨረታው ተሰርዞ ያሲያዙት ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግና እቃው በድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እንገልፃለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 0222 118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-07 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ምድብ 5%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T09:30:28.000Z
← Back to all tenders