Spare Parts and Car Decoration Materials

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ዕቃዎቹ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙናየተወረሱ ልዩልዩ ዕቃዎች

ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን

  •  የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣
  • ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣
  • የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችን፣
  •  የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፤
  • የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣
  • የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና
  • ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ዕቃዎቹ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም

  1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
  2.  በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4.  በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISS[OW ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFCE አሰርተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡-ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
  9.  ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  10. መ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤት

የጨረታው አይነት 

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና

የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ

ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

የእቃ ሐራጅ

 

እስከ 02/13/2018

03/13/2018 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የእቃ ግልፅ

እስከ 03/13/2018

04/13/2018 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ ፡ 011-470-85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀስበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጨ መንገድ መገንጪያ ፊት

ለፌት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-09 10:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia Custom Commission Akakai Kality Custom Branch Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:17:45.000Z
← Back to all tenders