Promotional Items

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት በተለያዩ ሎተሪዎች የቅስቀሳ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፊያ፣ የመኪና ቦሎ መለጠፊያ፣ ከረጢት፣ ዣንጥላ፣ ትንሹ ማስታወሻ ደብተር እና የማስታወቂያ ባንዲራ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/002/2019

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት በተለያዩ ሎተሪዎች የቅስቀሳ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ቲሸርት፣ ኮፊያ፣ የመኪና ቦሎ መለጠፊያ፣ ከረጢት፣ ዣንጥላ፣ ትንሹ ማስታወሻ ደብተር እና የማስታወቂያ ባንዲራ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ውድድር አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትድረስ በዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግዋናውን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታውመወዳደርይችላሉ። ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የቴክኒካልና ፈይናንሻል የመጫረቻ ስነዶቻችሁን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሊራንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን አሟልታችሁ እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-126 7816 ደውሎ መረዳት ይቻላል:።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-15 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
  • Bid bond: 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T15:01:51.000Z
← Back to all tenders