Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን ተንቀሳቃሽ የመያዣ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ከዚህ በታች ስማቸው የተገለፁት ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበደሩትን የብድር ገንዘብ በገቡት ውል መሠረት መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ለብድሩ አመላለስ በዋስትና የያዛቸውን ተንቀሳቃሽ የመያዣ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የመያዣ ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

.

የተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው/ ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሚሸጠው ንብረት አይነት

የመያዣ ንብረት ዝርዘር መረጃ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)

የሐራጁ ደረጃ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት

1

ቴዎድሮስ አያና

በጋምቤላ ///መንግስት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ

ትራክተር

ትራክተር ብራንዱ CASE ሞዴል 110JX የተመረተበት ዘመን 2015 ጉልበት 110HP

506,490.95

የመጀመሪያ

ጋምቤላ ዲስትሪክት /ቤት መስከረም 28 ቀን 2019 ከረፋዱ 400 እስከ 600

2

ጎይቶም ነጋ

በጋምቤላ ///መንግስት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ

ትራክተር

ትራክተር ብራንዱ CLASS ሞዴል 340C የተመረተበት ዘመን 2015 ጉልበት 110HP

416,406.25

የመጀመሪያ

ጋምቤላ ዲስትሪክት /ቤት መስከረም 28 ቀን 2019 ከቀኑ 900 እስከ 1100 ሰዓት

3

ሀሸንጌ አግሮ ቢዝነስ /የተ/የግ/

በጋምቤላ ///መንግስት ጋምቤላ ከተማ ባንኩ በተከራየው መጋዘን ቅጥር ግቢ

ሞተር ሳይክል

ሊፋን ፤የሞተር ቁጥር- A1446284 የሻንሲ ቁጥር- LF3YCK001AD000817

22,500.00

የመጀመሪያ

ጋምቤላ ዲስትሪክት /ቤት መስከረም 29 ቀን 2019 ከረፋዱ 400 እስከ 600

የሐራጅ መመሪያ

1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጅ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% /ሃያ አምስት በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.PO) በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ፡፡

2. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች ከድርጅቱ የተሰጠውን ውክልና እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡

4. በሐራጅ ሽያጭ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።

5.የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል።

6. በሐራጁ ለተሸናፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

7. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያን ጨምሮ ይከፍላል።

8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ/በካሽ ብቻ ነው።

9. ተጨማሪ መረጃ ማገኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት፤ በስልክ ቁጥር፡ +251 475 512 577፤ +251 475 512 588፤ ወይም +251 471 518 284 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

10. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም የሐራጁ ተሳታፊዎች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር የጉብኝት ፕሮግራም ቀጠሮ በማስያዝ ፕሮጀክቱን መጎብኘት ይችላል፡፡

11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-09 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
  • Posted at: 2026-09-03T08:22:57.000Z
← Back to all tenders