Plastic Products

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ለሚፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቤት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር/BG0/01/2019

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ለሚፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቤት እቃዎች ማለትም (1) ባለ 4 በ5 ሜትር 17 319 ፕላስቲክ ሺት (2) 17319 መካከለኛ ብረት ድስት ባለ 5 ሊትር፤ (3) 17319 ባለ 20ሊትር የውሃ ጀሪካን፤ (4) 17319 ፕላስቲክ ሰሀን እና (5) የሻይ ማንቆርቆሪያ(ባለ ሁለት ሊትር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-

1. ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት የሥራ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን ለማቅረብ የሚያስችል አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ለዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

4. የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 20 ብር 100 በመክፈል መውሰድ ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ማስገባት አለባቸው፡

6. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 675,000 (ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ) CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም የባንከ ጋራንቲ (ቢድ ሴኩሪቲ) ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ለብቻ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል።

7. ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ/የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ቅድሚያ ያስይዛሉ።

8. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 11 442 7770 ላይ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ- ሣሪስ አዲስ ጎማ ሆራይዘን ፋብሪካ ፊት ለፊት

ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ

ፊንፊኔ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Busa Gonfa Oromia
  • Buyer address: ሳሪስ አዲስ ጎማ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 675,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:21:09.000Z
← Back to all tenders