Disposal Sale
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሐግ/ ተሽጨ/ 01 /2018
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች አዲስ አበባ ከተማ ላይ ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተራ ቁጥር |
ለጨረታ የቀረቡት ተሽከርከሪዎች ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
ዴው ሴየሎ ሴዳን (DAEWOO CIELO sedan) |
4 |
|
2 |
ዴው ዳማስ ቫን (DAEWOO DAMAS Van) |
2 |
|
3 |
ዴው ቲኮ ኮምፓክት (DAEWOO TICO COMPACT) |
14 |
|
4 |
ኪያ ፕራይድ ኮምፓክት(KIA pride COMPACT Carburetor) |
3 |
|
5 |
ኪያ ስፖርቴጅ (KIA SPORTAGE SUV PASSANGER |
3 |
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች አዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 10፣ ቤት ቁጥር 198፣ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ የድሮው ታይዋን ገበያ መንገድ ባለበት መስመር በሚገኘው ቤዛ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ከሰኞ -ቅዳሜ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር፤ 1000004330793 ገቢ በማድረግ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመክፈል፣ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ በሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ደረሰኙን በማቅረብ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች አንድ እና ከዛ በላይ ተሽከርካሪ ተወዳድረዉ መግዛት ይችላሉ። ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል በመሙላት ከ10% (አስር በመቶ) የጨረታና ውል ማስከበሪያ C.P.O. ጋር አያይዘዉ በሰም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 5058፣ ቦሌ ሚኒ አጠገብ ከሚገኘው ሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታዉ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም፣ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ/ በተገኙበት በሴቪታ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።
5. ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት አለዉ።
6. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡ 011 663 9191 EXT.257/260 ደዉለዉ ማግኘት ይችላሉ።
ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ሐግቤስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
- Bid bond: 10% ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T09:12:47.000Z
- Source: 2merkato