Disposal Sale
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. በአሁኑ ወቅት በዋና ቢሮ (Head Office) እየተጠቀመባቸው ያሉትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ ለሁለተኛ ግዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢጠመ/0006/2018
ኩባንያችን የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ በአሁኑ ወቅት በዋና ቢሮ (Head Office) እየተጠቀመባቸው ያሉትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎች ለመግዛት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪዎች አይነት በዝርዝር |
ብዛት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
ሲሲ |
የሠሌዳ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
ሚኒባስ ሃዩንዳይ (MIN BUS H-1) |
1 |
D4BHG009026 |
KMWA37HAGU835241 |
2476 |
03-አ36111አአ |
2,750,000.00 |
|
2 |
ክሬታ-ሃዩንዳይ |
1 |
G4FGGU832055 |
MALC381CBGM133356 |
1591 |
03-አ37413አአ |
3,250,000.00 |
|
3 |
ክሬታ-ሃዩንዳይ |
1 |
G4FGGU847434 |
MALC381CBGM133346 |
1591 |
03-አ37414አአ |
3,250,000.00 |
|
4 |
ቺቭሮሌት |
1 |
B12D1386347KD3 |
KL1TJ6CD8GB514647 |
1200 |
03-አ38578አአ |
1,350,000.00 |
ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡-
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 2 ላይ በተገለጸው መሰረት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋት 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ለሽያጭ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጆሳንሰን አካባቢ በሚገኘው የኩባንያዉ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 7ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት የጨረታ ስነዱን በመውሰድ ተሽከርካሪዎቹን መመልከት ትችላላችሁ።
2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በኩባንያችን ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ጨረታዉ ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታዉ መገምገሚያ መስፈርት መኪናዉን ለመግዛት የቀረበ ዋጋ፣ የተሟላ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ስ.ፒ.ኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነዉ።
4. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለጸዉን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላስያዘ እና የተዘረዘሩትን ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉድቅ ይደረጋል።
5. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማለትም ከሰኞ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛዉ ቀን ማለትም ሰኞ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በኩባንያዉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቹ በራሱ ዉሳኔ ጨረታዉ በሚከፈትበት ጊዜ ሳያገኝ ቢቀር የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉልም።
6. በጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታዉን ማሸነፋቸዉ ከተነገረበት ወይም የስማቸዉ ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ2 /ሁለት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የወል ማስከበሪያ የዉል ዋጋዉን 10 በመቶ በማቅረብ ኩባንያዉ ጋር ወል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ መክፈል ይኖርባችዋል:: ሆኖም ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ዉል ካልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያዉን በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያዉ ገቢ ይደረጋል።
7. የጫረታዉ አሸናፊ ከሚገዛዉ ተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ ማናቸዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ የስም ማዘዋወሪያ ተሽከርካሪ የዋጋ ግምት እንዲሁም በመንገድ ትራንስፖርት በኩል ሊፈጠር የሚችለዉን ማናቸዉንም ወጪዎች ይክፍላል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች በ5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ መዉሰዳቸዉ ሲረጋገጥ ያስያዙት የዉል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. ተጫራቾች የፋይናንስ ዋጋ ግምገማ (Financial Proposal) ሰነድ በታሽገ ፖስታ በሚከተለው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስታወቂያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ
የሰው ሃብትና ተቋም አገልግሎት
ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09፣ ጆሳንሰን አካባቢ
ከኖቢ ኮምፕሌክ ህንጻ አጠገብ በሚገኘው
የኩባንያዉ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፡ +251-115 57 57 57
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
10. የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ኢማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ስለ ጫረታዉ አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ጫረታዉ ከመዘጋቱ ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115 57 57 57 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-28
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-28 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Reinsurance Share Company
- Buyer address: አፍሪካ ጉዳና ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T11:09:21.000Z
- Source: 2merkato