Equipment and Accessories
ብርሃን ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Addis Ababa
Description
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ-03/19
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ. |
ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶች ዝርዝር |
|
1 |
ያገለገሉ ዴስክቶፕ ኮምፕዩተሮች |
|
2 |
ያገለገሉ የቢሮ ማሽኖች /office equipment/ |
|
3 |
ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች |
|
4 |
ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማ እና ባትሪዎች |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ የቢሮ መጠቀሚያ ኢኩፕመንቶች፣ የቢሮ መጠቀሚያ ፈርኒቸሮች እና ሌሎች እቃዎች ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል::
- ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ንብረቶች ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት ባቡር ጣቢያ መጨረሻ በተለምዶ ሰማያዊ ሕንፃ ተብሎ የሚጠራዉ ሕንጻ ባለበት በኩል በስተቀኝ ባለዉ መንገድ ወደ ዉስጥ ገብተዉ የግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ድርጀት ሕንፃ አጠገብ በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ : ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድካ ግቢ ዉስጥ 2 ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ሊገዙት ያሰቧቸዉን ያገለገሉ የቢሮ ኢኩፕመንቶች ፈርኒቸሮች እና ሌሎች እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስክበሪያ ገንዘብ በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ያገለገሉ የቢሮ ኢኩፕመንቶች ፈርኒቸሮች እና ሌሎች እቃዎች ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ CPO ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታዉ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል::ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን ያገለገሉ የቢሮ ኢኩፕመንቶች ፈርኒቸሮች እና ሌሎች እቃዎች ባቀረቡት ነጠላ ዋጋ መሰረት በአጠቃላይ ብዛቱ ተባዝቶ ጠቅላላ ዋጋዉን በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በአስር ቀን ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል:: ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል::
- ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918890721/0114437439/ 0116631729 ይደውሉ::
Tender details
- Deadline: 2026-10-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-02 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Berhan Bank S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T12:33:00.000Z
- Source: 2merkato