Products and Services
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለሚፈናቀሉ ዜጎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል 50000 ኩ/ል(ሃምሳ ሺህ ኩንታል) አዳማ እና 50000 ኩ/ል(ሃምሳ ሺህ ኩንታል) ስንዴ ሻሸማኔ በሚገኘው መጋዘን ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር/BGO/02/2019
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለሚፈናቀሉ ዜጎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል 50000 ኩ/ል(ሃምሳ ሺህ ኩንታል) አዳማ እና 50000 ኩ/ል(ሃምሳ ሺህ ኩንታል) ስንዴ ሻሸማኔ በሚገኘው መጋዘን ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች
1. ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት የሥራ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ለማቅረብ የሚያስችል አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸዉን የሚገልጽ ለዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 20 ብር 250 በመክፈል መውሰድ ያለባቸው ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
6. ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ/ የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ቅድሚያ ያስይዛሉ።
7. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 114 427 770 ላይ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ - ሣሪስ አዲስ ጎማ ሆራይዘን ፋብሪካ ፊት ለፊት
ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ
ፊንፊኔ
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛ ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Busa Gonfa Oromia
- Buyer address: ሳሪስ አዲስ ጎማ ፊት ለፊት
- Bid document price: 250.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T10:59:22.000Z
- Source: 2merkato