Printing and Publishing
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የተለያዩ ህትመት ስራዎችን በብራንዱ መሰረት ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የተለያዩ ህትመት ስራዎችን በብራንዱ መሰረት ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድሞር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መውሰድ ይቻላል፡፡ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተሞ፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በስዓቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በሰአቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚፈለጉትን የህትመት ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-22 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Media Corporation
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T13:17:17.000Z
- Source: 2merkato