Plastic Products
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደዌ ሀረዋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Plastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw Materials
Amhara
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesComputer and AccessoriesIT and TelecomEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureCleaning and Janitorial Equipment and ServiceVehicle (garage service)Maintenance and RepairFuel and LubricantsWater Pipes and FittingsConstruction and Water WorksBuilding and Finishing MaterialsSanitary and CeramicsSpare Parts and Car Decoration MaterialsAmharic2merkatoበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደዌ ሀረዋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደዌ ሀረዋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለሁለተኛ ዙር በ2019 የበጀት ዓመት ለደ/ሀ/ወ/ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1: የተለያዩ የውሃ እቃዎች ፣
- ሎት 2: አላቂ/የጽሕፈት እቃዎች
- ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 4፦ ቋሚ የቢሮ እቃዎች የሀገር ውስጥ፣
- ሎት 5፦ ቋሚ የቢሮ እቃዎች የውጭ፣
- ሎት 6፦ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 7፡ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ የሰርቪስ መለዋወጫዎች ለ6 ወራት የሚቆይ፣
- ሎት 8፡-በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
- የሎት 9፡ የልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች የጌጣጌጥ /የዲኮር/ ዕቃዎች 6 ወራት የሚቆይ፣
- ሎት10፡- ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ዘይትና ቅባቶችን፣
- ሎት 11፦ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ከነከላማደሪያቸው እና
- ሎት 12፡-ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ የሞተር፣ ካምቢዮ፣ የቦዲ እና ሌሎችም መለዋወጫዎች ለ6 ወራት የሚቆይ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-
- ለሥራው በእያንዳንዱ ከላይ በተጠየቀው ዘርፍ/ሎት ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የግብር ክሊራንስ ያለው ለእያንዳንዱ ሎት የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከአምስት መቶ ሺ /500ሺ /ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የጨረታውን ሰነድ ከደ/ሀ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7/ሰባት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘውትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር /200/ ሁለት መቶ /ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ በደ/ሀ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አንድ /11/ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡02 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ጽ/ቤቱ ጨረታውን የምንገመግመው በጠቅላላ ድምር ውጤት ሲሆን ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ሁሉምእቃዎች መሙላት ግዴታ ነው፡፡ በየሎቶቹ የየራሳቸውን የግዥ መመሪያ ሰነዱን ስንሸጥ የምናያይዝ ይሆናል ማንኛውም ተጫራች መመሪያ ከሰነዱ ጋር መኖሩን አረጋግጦ መግዛት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡-ሰላሳ ሺህ ብር (30,000)፣ ለሎት 2፡-ስልሳ ሺህ ብር (60,000) ፣ለሎት 3፡-ሰላሳ ሺህ ብር (30,000)፣ ለሎት 4፡- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) ለሎት 5፡- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) ፣ለሎት 6፡- አስራ አምስት ሺህ ብር (15,000) ፣ለሎት 7፡- ሰባ ሺህ ብር (70,000) ፣ለሎት 8፡- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) ፣ለሎት 9፡- አምስት ሺህ ብር (5,000) ፣ለሎት 10፡- ሰላሳ ሺህ ብር (30,000) ፣ለሎት 11፡- አምሳ ሺህ ብር (50,000) እና ለሎት 12፡- አርባ ሺህ ብር (40,000) በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መሂ አንድ(1)ገቢ በማድረግ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee/ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10%(አስር ፐርሰንት)በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንከ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /uncondition bank guarantee/ ማስያዝ አለባቸው።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች የደ/ሀ..ወ/ገ/ጽ/ቤት/ የጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ያስረክባል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ፊርማቸውን፣እንዲሁም ሙሉ አድራሻቸውን መግለጽ እና ማህተም መምታት አለባቸው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ ከ/ደ/ሀ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግንባር በመቅረብ ወይንም
- በስልክ ቁጥር 0956695575/0911596161/0953047604/0920405661/0913080626/0913212411 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት በግልጽ ይከፈታል።
የደዌ ሀረዋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
/ቦራ/
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 10:02
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡02 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-21 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ልዩ ዞን የደዌ ሀረዋ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:11:56.000Z
- Source: 2merkato