Others

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛው በውሉ መሰረት የኪራይ ክፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ ማምረቻ ማሽነሪ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል።

.

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የዝግ ጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

ዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ

የዝግ ጨረታ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የጨረታ ሁኔታ

1

አቶ ሱማሞ ዶባሞ ኢርግቾ

1. Rotary Oven 16 Try (01) set 2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set. 3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set 4. Molding machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) set 5. Brade slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) set 6. French read tray and rottey for ATDF250 ሁለት (02) set 7. Flat tray with Trolley for ATDF 250 ሁለት (02) 8. Diesel Generator አንድ (01) set ናቸው፡፡

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (በተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤

9,792,010.52

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ክልል ውስጥ በተቋቋመው በአቶ ሱማሞ ዶባሞ (የተከራይ) የዳቦ ማምረቻ ቦታ፤

ጥቅምት 03 ቀን 2019 . 400 እስከ 600

ዝግ ጨረታ

የዝግ ጨረታው መመሪያ

1. በዝግ ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻ በመጥቀስ፤ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፤ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገዢው የሚገዛበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል።

2. ንብረቱ የሚገኘው ሆሳዕና ከተማ አስ/ር፤ በአራዳ ቀበሌ ውስጥ በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት በሕግ የተወሰነ ታክስ ጨምሮ የሚጠየቁ ማንኛውንም ክፍያ በቅድሚያ በመከፈል ንብረቱን ይረከባል።

3. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን ይረከባል። በዝግ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በዝግ ጨረታ መሳተፍ ይችላል።

4. ንብረቱን በከፊል ለመከራየት የሚፈልግ ተጫራች ከሆነ ቢያንስ ያሸነፈበትን ዋጋ 20% ቅድሚያ በመከፈልና የባንኩን የሊዝ ኪራይ መስፈርት በሟሟላት በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የዝግ ተጫራች አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች በጨረታው ያስያዙት የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

5. ንብረቱ በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክቱ ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች መስማማት ይጠበቅበታል፡፡ የዝግ ጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጠበቅበታል።

6. የዝግ ጨረታ አሸናፊ የካፒታል ዕቃው ካለበት ቦታ ወደ ሚፈለግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፤ የጉዞ ኢንሹራንስ፤ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው ይከፍላል።

7. የዝግ ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢትዮጰያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ሎን ወርክአውት ዲቪዥን ቢሮ ይደረጋል፡፡ ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪከት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528/38 ደውሎ ማነጋገር ይችላል። ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጨራች ከዝግ ጨረታ ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በተከራይ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የዝግ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-10-13 12:00
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:53:34.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders