Equipment and Accessories
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎችን እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን እና የቢሮ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 159/2018)
- ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ አካሎችን እንዲሁም
- ኩባንያው ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎችን እና የቢሮ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብርና ሌሎች ዕዳዎችና ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናል።
የተሽከርካሪ የስም ዝውውር በገዢ ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ቢቆይ በዚህ ምክንያት ለሚመጣ ችግር ኩባንያችን ኃላፊነት አይወስድም።
አሸናፊ ተጫራች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TN No.) ማቅረብ ይኖርበታል።
1. ንብረቶቹ የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፡- ገላን ሪከቨሪ ፡ ገላን ኖክ ፊት ለፊት
ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ መውሰድ ይችላል።
የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን፤ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ (ት ሳይጨምር) በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ ከመቶ) በኩባንያው ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ ምድር ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨመር መሆኑን እንገልፃለን።
ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ 21ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና 5 ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል። ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 011-442-14_99/09-11-82-05-76/ በመደወል መጠየቅ ይችላል::
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-09-22 09:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Reporter (Sep 13, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T10:52:16.000Z
- Source: 2merkato