Other Sales

በአብክመ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዊ/ብሔ/አስ/ዞን/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት የአን/ጓ/ወ/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት በአገዉ ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር በሀተታ ቀበሌ በእኩት ን/ቀበሌ ልዩ ስሙ ዛኸንፃ ላይ የሚገኘውን የማህበረሰብ ባህርዛፍ፤ ዲከረንስ ግራር እና የፈረንጅ ፅድ በግልፅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአዊ/ብሔ/አስ/ዞን/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት የአን/ጓ/ወ/ አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት በአገዉ ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር በሀተታ ቀበሌ በእኩት ን/ቀበሌ ልዩ ስሙ ዛኸንፃ ላይ የሚገኘውን የማህበረሰብ ባህርዛፍ፤ ዲከረንስ ግራር እና የፈረንጅ ፅድ በግልፅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፤ ባህርዛፍ በቁጥር 1967 ሲሆን መነሻ ዋጋ 1,937,700 ብር፣ ዲከረንስ ግራር በቁጥር 4896 ሲሆን መነሻ ዋጋ 2,496,850 ብር እና የፈረንጅ ፅድ በቁጥር 832 ሲሆን መነሻ ዋጋ 1,376,700 ብር አጠቃላይ የመነሻ ዋጋ 5,811,250 ብር ፤የጨረታ ማስከበሪያ 581,125 (አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃያ አምስት) ብር ሲሆን። የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በአጣና ግንዲላ ወይም በጣዉላ ንግድ የተሰማሩ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በዘመኑ ግብር ከፍለዉ ያጠናቀቁ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የደን ዉጤቱን የሚገዙበት ክልል መነሻ በማድረግ በመመሪያዉ መሰረት የሚከፈሉባቸዉ የደን አይነቶች የዋጋ መጠን ግልፅ በሆነ ጽሁፍ በትክክል ሞልተዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርቲፊኬት፣ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5.  የጨረታዉ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዋጋ አስራ ሶስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ ቅድሚያ መክፈል ይኖርባቸዋል።
  6. ለጨረታ የሚቀርበዉ ዋጋ መግለጫ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሆኖ በተጫራቹ በራሱ ወይም በህጋዊ ወኪል አማካኝነት ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎበት መቅረብ ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ካለም ዋጋዉን በሞላዉ ሰዉ ፓራፍ መኖር አለበት።
  7. ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ባህርዛፍ፤ ዲከረንስ ግራር እና የፈረንጅ ፅድ በሀተታ ቀበሌ በእኩት ን/ቀበሌ ልዩ ስሙ ዛኸንፃ ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ።
  8.  ለጨረታዉ የሚቀርበዉ ዋጋ እስከ 90 ቀናት ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. የጨረታው ተወዳዳሪ በጨረታ ሳጥን የመወዳደሪያ ዋጋ የማስገቢያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ዋጋን መለወጥ ማሻሻል ወይም በጨረታ አልካፈልም ማለት አይችልም። አልካፈልም ብሎ ካወጣም የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አገ/ግ/ከተ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በከተማ አስተዳደሩ የገቢ ደረሰኝ በመሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አገ/ግ/ቤት ከ/አሰ ገንዘብ /ጽ/ቤት ወይም ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ21ኛ ቀን እስከ ከጥዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሣጥን ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ማንኛዉም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  14. የጨረታዉ አሸናፊ ከታወቀ በኋላ አሸናፊ ላልሆኑት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
  15. በጨረታው አሸናፊ የሆነው አሸናፊ መሆኑ በተገለፀበት እስከ 15 ቀን ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የዋጋዉን አስር በመቶ የስራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ቀርቦ ዉል ይፈርማል።
  16. የዉል ግዴታዉን ያልተወያልተወጣ ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል ተጨማሪ ጉዳት ካደረሰ በህግ ሊጠየቅ ይችላል።
  17.  አሸናፊው ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስልት ዉሉን ፈፅሞ የግዢዉን ዋጋ ከከፈለ በኋላ ነዉ።
  18. የመጫረቻ ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል። በተሞላዉ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተሞላዉ እና በነጠላ ዋጋ ላይ የተቀመጠዉ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  19. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አገ/ግ/ከተ/አስ/ገንዘብ /ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 02 በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጥዋቱ 4፡15 ታሽጐ ከጥዋቱ 4፡30 ይከፈታል፤ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 19 44 71 23 /09 23 52 45 59 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  22. ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ኮሚቴ የቆጠረዉን ባህርዛፍ፤ዲከረንስ ግራር እና የፈረንጅ ፅድ ደን የጨረታ ሰነድ ከመግባቱ በፊት በትክክል ቆጥረዉ
    መወዳደር ይችላሉ፤ አሸናፊው የሚለየዉ በሶስቱም ዛፍ አይነቶች ጠቅላላ ድምር ከፍተኛ ዋጋ ያስገባ ብቻ ይሆናል፡፡

የአን/ጓ/ወ/አካ/ጥ/ተጠሪ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-05
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጥዋቱ 4፡15
  • Bid opening: 2026-10-05 12:00
  • Bid opening (note): በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጥዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአን/ጓ/ወ/አካ/ጥ/ ተጠሪ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Sep 14, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T13:14:52.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders