Disposal Sale

አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቬኮ እንዲሁም በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽያጭ/0006/2026

አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቬኮ (Model 50C15/E3 Year 2020፣  Chassis no EBPBCAHAALD000015 እና EBPBCAHAAD000016፣ Motor no: FICE3481J3827324 እና FICE3481J 3827326፤ Clour: White፣ Vehicle type: Bus፣ CC: 2998 እንዲሁም በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ቻንሲ ቁጥር LCN64ED50M0097133፤ የሞተር ቁጥር LFB479Q-170300359* ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ።

1. ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ውጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡

5. ጨረታው አሸናፊ ለተሽከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ክፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል፡፡

6. ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

7. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘውን ገንዘብ አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፣

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ /ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።

11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው፡፡

12. የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡

13. የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡

14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0984 551 186 / 0973 300 059

አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-06 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 21, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T09:04:38.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders