Other Sales

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት የቁም ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ

የቁም ደን ሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OFWE/GU-02/2019

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ጅባት ጌዶ ድስትሪክት፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጋራሙልታ እና ጀርሶ ጉርሱም ዲስትሪክቶች ፤ ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ስግሞ ሰጠማ እና በቢያ ፎላ ዲስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንድላ፤ በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ድስትሪክቶች ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የ”Gravelea robusta” ግንድላ እና ባሌ ቅ/ጽ/ቤት አሎሼ ባቱ ድስትሪክት ላይ የፈረንጅ ጥድ እና የባህር ዛፍ ድብልቅ ግንድላ እንዲሁም ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ሲቦ ቶሊ ቆቦ ድስትሪክት ላይ የዝርያዎች ድብልቅ ግንድላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TIN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ፈንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት ፊንፊኔ ከተማ፤ ባሌ ቅ/ጽ/ቤት ጎባ ከተማ ፤ ወለጋ ቅ/ጽ/ቤት ጊምቢ ከተማ፤ ሀራርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ እና ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት ይቆይል።
  3. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፣ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  5.  ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111240249 በመደወል መጠየቅ ወይም www.oromiaforest.et  ድህረ ገፅ ማጎብኘት ይችላሉ።

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታተይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-10-06 17:00
  • Bid opening (note): ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Forest and Wildlife Enterprise
  • Buyer address: አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 22, 2026)
  • Posted at: 2026-09-22T12:58:27.000Z
  • Buyer website: https://www.oromiaforest.gov.et
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders