Disposal Sale
የመቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን ንብረትነቱ የራሱ የሆነ ያገለገለና የሚሠራ ብዛት 1 (አንድ) የሆነ ሲኖ ትራክ መኪና ጋቢናውንና ተሳቢውን የነዳጅ ታንከር ቦቴ (ሎቤድ) በአንድ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የ3ኛ ዙር የመኪና ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የመቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን ንብረትነቱ የራሱ የሆነ ያገለገለና የሚሠራ ብዛት 1 (አንድ) የሆነ ሲኖ ትራክ መኪና ጋቢናውንና ተሳቢውን የነዳጅ ታንከር ቦቴ (ሎቤድ) በአንድ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ በመነሻ ዋጋ ከቫት በፊት በ10,000,000.00 (አሥር ሚሊዮን) ብር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. የመኪናው ሰሌዳ ቁጥር (prole)
የጋቢናው ሰሌዳ ቁጥር ET-3-43263 ሞዴል ZZ425753241v የተሰራበት ሀገር ቻይና የተሰራበት ዘመን 2009 G.C የሻንሲ ቁጥር LZZ5CL51329A429807 የሞተር ቁጥር 091107021647
2. የተሳቢው ወይም የቦቴ ሰሌዳ ቁጥር
የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር ET-3-14302 ሞዴል MIE/36H/fTL/3/12.5 የተሰራበት ሀገር ኢትዮጵያ- መስፍን ኢንጂነሪንግ የተሰራበት ዘመን 2009 G.C የሻንሲ ቁጥር CTS-496-09 ቦቴ የመጫን አቅም 50,000 ሌትር መሆኑን እየገለፅን፡-
ተጫራቾች ማሟላት ያላበቸው ዋና ዋና መስፈርቶች:
1. ማንኛውም ተጫራች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ወይም የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም ኅ/ሥ/ማህበራት ከሆኑ በአዋጁ መሰረት የተቋቋመበት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ወይም TIN NUMBER ያላቸው መሆን አለባቸው።
3. ከመንግስት ግብር (ዕዳ) ነፃ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
4. ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ በሰም በተሸገ ፖስታ የድርጅቱ ከብ ማህተም ያረፈበት አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት።
5. የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋጋ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር ማስያዝ አለበት።
6. የጨረታው ሰነድ የሚሸጠው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ተሸጦ የጨረታው ቀነ ገደብ ካለቀ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰናዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለዚሁ ዓለማ በተዘገጀው የጨረታ ሳጥን ገብቶ ሳጥኑ ይታሸግና በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ እና ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል። የቴክኒክ ሰነዱ በቅድሚያ ይታይና ቴክኒኩን ያላለፈ ወገን የፋይናንሻል ሰናዳቸውን ሳይታይ ከጨረታ ውጪ ሆኖ ሰነዱ ተመላሽ ይሆናል። ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ከላው ተቀባይነት አይኖረውም።
7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ ጥያቄ፣አስተያየት፣ማስተካከያ ካለው የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ብቻ ለድርጅቱ በጽሁፍ ማቅረብ አለበት። በዚሁ አግባብ ድርጅቱም ተመሳሳይ ጥያቄ ካለው የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ለተጫራቾች ማሳወቅ አለበት። የጨረታ ሰነድ ቋንቋ የሚቀርበው በአማርኛ ይሆናል።
8. የጨረታ ማስከበሪያ CPO 500,000.00 (አምሥት መቶ ሺህ ብር) በዩኒየኑ ሙሉ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሒሳብ ቁጥር 1000041208434 / በኦሮሚያ ሕ/ሥራ ባንክ በሒሳብ ቁጥር 1000006718586 እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያና ደንብ መሰረት በተቋቋመ ማንኛውም ባንክ ማስያዝ ይችላሉ።
9. መኪናውን በተመለከተ ውዝፍ የመንግሥት ግብር በዩኒየኑ ወጪ የሚሸፈን ሆኖ የሥም ማዛወሪያ ክፍያ ተጫራቹ የሚሸፍን ይሆናል።
10. ማንኛውም ተጫራች ሁለቱን መኪና ነጣጥሎ መጫረትና መግዛት አይቻልም፡፡ እንዲሁም ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታውን አስገዳጅ ህግ የማይወጣ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 218/2011 እና በሕብረት ሥራ ማህበራት ግዥ መማሪያ ቁጥር ደ/ገ/007/2017 መሰረት ድርጅቱ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ያሳውቃል።
11. የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከታወቀ መኪናውን ሙሉ ክፍያውን በአንድ ጊዜ በዩኒየኑ ከላይ በተጠቀሰው ሒሳብ ቁጥር በማስገባት መኪናውን እስከ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማንሳት አለበት። ከተወሰነው ቀን ካለፈ ተጫራቹ ለዩኒየኑ ቅጣት በየቀኑ 2,000.00 (ሁለት ሺህ) ብር ለመክፈል በህግ ፊት የሚፀናና የሚገደድ ይሆናል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ ፊት የተጠበቀ ነው።
የጨረታ ማስረከቢያ አድራሻ - በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሸዋ ዞን፤ ዱግዳ ወረዳ፤ መቂ ከተማ
መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን (ቢሮ ቁጥር-2) ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 022-118-1402 / 09-09-34-34-34 / 09-10–92–95-36 /09-20-36-80-41 መደወል ይቻላል።
E-mail [email protected]
የመቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-10-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-13 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Meki Batu Horticultural producers Union
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 24, 2026)
- Posted at: 2026-09-24T07:54:51.000Z
- Source: Qelal Tenders