Textile, Garments and Uniforms

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 02/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 02/2018 በ25/01/2019

  • የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ግላሶች እና ከቨሮች፣
  • የእጅ ሰዓቶች፣ ስፔርፓርቶች፣ የእይታ ዕቃዎች/መነፅሮች፣ መሬት ምንጣፍ፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣
  • የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ የእስፖርት መስሪያ መሳሪያዎች፣ ኳስ፣
  • የተለያዩ አርትፍሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1.የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።

2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ሙድአነኖ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነድ ለመግዛት ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።

5. ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

6.ተ ጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

7. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

8. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያው መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።

9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

12. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ /ጽ /ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-05
  • Bid closing time: 08:00
  • Bid opening: 2026-10-05 10:00
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 26, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T08:06:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders