Other Sales

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውን እና በሰንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፤ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 7፤ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን የጨረታ ክፍል ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 1153 እና 011 515 0711 ኢአ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.ሜ

የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት ኣድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

 

የምዝገባ ሰዓት

 

የጨረታ ሰዓት

 

1

አቶ አበበ ሞሲሳ ባይሳ

አቶ አበራ ደፋር ከተማ

ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል ህንፃ /መጋዘን/፣ G+2 ቢሮ እና G+1 የጥበቃ ቤት ያለው

10,094.13

 

OR00309 5212003

ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ

170,970,819.78

 

ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም

4:30-5:30

 

5:30-6:00

 

2

አቶ አበበ ሞሲሳ ባይሳ

ኤጂኤም/AGM/ኢንዱስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል ህንፃ መጋዘን፣ G+1 ቢሮ እና G+1 ሁለት የጥበቃ ቤት ያለው

10,222.12

 

OR0001 1323028008

ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ፣ መልካ ኖኖ ክ ከተማ ረታበት ታጠቅ አካባቢ

201,704,931.59

 

ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም

 

8:30-9:30

 

9:00-10:00

 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-29
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-29 16:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 27, 2026)
  • Posted at: 2026-09-28T14:30:55.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders