Disposal Sale

ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታማስታወቂያ

ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለቡት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪዎቹ በሚገኙበት አድራሻ በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል በሙልሙል ዳቦ በኩል ወረድ ብሎ ከጋና ኢምባሲ ፊትለፊት ወይም ኬር ኢትዮጵያ ጎን ባለው ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ ቢሮ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 / 8:00 እስከ 10፡00 ሰአት ድረስ፤ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 መመልከት ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
  4. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፓስታ/ በአዲስ አበባ ብስራተ ገብራኤል ከጋና ኤንባሲ ፊትለፊት ወይም ኬር ኢትዮጵያ ጎን በሚገኘው ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ መስሪያቤት እንግዳ መቀበያ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታውን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ነገር ግን በሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአፍሮ ቴንደር፡ 2መርካቶ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው።
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎችን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከተታይ የሥራ ቀናት በአዲስ አበባ፤ ፓዝፋይንደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  8. የጨረታ መዝጊያ ቀን ጥቅምት 11 ፣ 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡00 ሰኣት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ብስራተ ገብራኤል ከጋና ኤንባሲ ወይም ኬር ኢትዮጵያ ጎን በሚገኘው በፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ መስሪያቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0113203501፣ 0996554526 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-10-21 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Pathfinder International Ethiopia
  • Buyer address: Old Airport area, behind the South African Embassy
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 30, 2026)
  • Posted at: 2026-09-30T12:46:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders