Other Sales
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ የግብርና ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የሽያጭ መለያ ቁጥር 07/002/2019 ዓ.ም
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2016/17 ያመረተዉን 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 17.48 ኩንታል እና በ2017/2018 3ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 25.49 (ሀያ አምስት ኩንታል ከ49/100)፤ አዶሻ ገብስ 380(ሶስት መቶ ሰማንያ ኩንታል)፤ ኪንግ በርድ ስንዴ 82(ሰማንያ ሁለት ኩንታል)፤ ትራቭለር ገብስ 200(ሁለት መቶ ኩንታል)፤ ኢቦኒ ገብስ 317(ሶስት መቶ አስራ ሰባት ኩንታል)፤ ሄነሪኬ ገብስ 24(ሀያ አራት ኩንታል)፤ አሩሶ ገብስ 16(አስራ ስድስት ኩንታል) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች እና ግዴታዎችን በማሟላት ዳደር ይችላሉ።
1. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ/የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት የሥራ ንግድ ፍቃድ፤ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ/የምስክር ወረቀት / ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ምርት የሰጠውን ጠቅ/ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዋስትና ገዜወ ከ2(ሁለት)ወር ያላነሰ የባንክ ዋስትና /CPO/ በኮሌጁ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ የትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት በ5 (አምስት) ቀናት ወስጥ የውል ስምምነት ካልፈጸመ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል።
4. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከአጋ/ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ እና አዲስ አበባ ሀይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንጻ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደወ መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አላጌ/ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ)ብር በስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውሥጥ መግዛት ይቻላል፤ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒዉን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፤ እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒዉን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከፍ ብሎ በተጠቀሰዉ አድራሻ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ ሆኖ ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም በተጨማሪም ኮሌጁ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የምርቱን ናሙና ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባሌ አጋርፋ የግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አጋርፋ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በኮሌጁ እህል መጋዘን ማየት ይችላሉ።
9. ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 662 5004 አዲስ አበባ ወይም 09 11 49 08 70 / 09 30 10 80 07 እና 09 22 31 92 74 አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ደውለዉ መጠቀም ይችላሉ።
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-10-13
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-13 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Oromia
- Publishing entity: Agarfa Agricultural TVET College
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 02, 2026)
- Posted at: 2026-10-02T07:44:43.000Z
- Source: Qelal Tenders