Spare Parts and Car Decoration Materials

አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የቶዮታ፣ ኪያ፣ ፎርድ፣ ኒሳን፣ ቢኤም ደብሊው እና ላንድሮቨር የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን (Spare Parts) በክፍት ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር የቶዮታ፣ ኪያ፣ ፎርድ፣ ኒሳን፣ ቢኤም ደብሊው እና ላንድሮቨር የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን (Spare Parts) በክፍት ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በዘርፉ ልምድ ያላቸው ወይም ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቱሪስት ቅርንጫፍ (አካውንት ቁጥር 1000003782968) በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት አምስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጀርባ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር፣ የምስክር ወረቀት ካለ ወይም የታደሠ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5 የጨረታ ዋጋው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡

6. ተጫራቾች እቃዎቹን አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 1372 አምስት ኪሎ ከአንበሳ ግቢ ጀርባ በሚገኝው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት መጋዘን በመገኘት የንብረቶቹን ሁኔታ በአካል መመልከት ይችላል።

7. ግልጽ ጨረታው መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች እቃዎቹ ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት እና እቃዎቹን በአግባቡ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

9 ድርጀቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር 0911 244 680 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አፍሪካን ሌክስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-09 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: African Lakes Ethiopia
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 03, 2026)
  • Posted at: 2026-10-05T11:21:18.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders