Spare Parts and Car Decoration Materials
አዋበል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የመኪና ዲኮርና ጌጣጌጥ እና የመኪና ዘይትና ቅባት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን/አዋበል/ወረዳ ፕ/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፣
- ሎት2 የመኪና ዲኮርና ጌጣጌጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ እንዲሁም
- ሎት3. የመኪና ዘይትና ቅባት ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈትሮች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ግብር ለመክፈሉ የሚያጋግጥ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የጨረታ ተሳታፊዎች የሚሞሉት ዋጋ ከ500000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫትVAT ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ተሳታፊዎች የሚሞሉት ዋጋ ከ500000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት VAT) ጨምሮ እንደተሞላ ተደርጎ ይያዝለታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፍኬሽን/ ከእያንዳንዱ ሎት /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የመሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ሎት 2 እና ሎት 3 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/፤ በመሂ አንድ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድርስ በጽ ቤቱ በግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587720630/0004 በመደወል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ሲከፈትም ሆነ ከተከፈተ በኋላ የሚገኝ ከጥቃቅን ስህተቶች በስተቀር ከባድ ስህተቶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የእቃው ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ እስፔስፊኬሽን ቀይሮ መሙላት የተከለከለ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
- አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎችን አዋ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ድረስ ያለማንጠባጠብ አጠቃሎ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- አሸናፊው በሎት ይለያል፤ በሎቱ ውስጥ የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ ዋጋቸው መሞላት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም የሚቀርበው እቃ ኦርጅናል መሆን አለበት።
- የመኪና መለዋወጫ እቃ አሸናፊ የሆነ አካል ወይም ድርጅት አገልግሎቱን ወይም ግዥዉን በዉሉ መስርት እስከ ሰኔ 30/2019 አ/ም ድርስ ማቅረብ ወይም መፈፀም አለበት።
- ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች ካሉ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018ዓ/ም መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- የሚመጡ ወይም የሚቀርቡ እቃዎችን ከተረጋገጠ በኋላ በየ ንብረት ክፍሉ ያደርሳል።
በምስ/ጎ/ዞን አዋበ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
ሉማሜ ፣
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 3፡30
- Bid opening: 2026-10-21 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: East Gojam Administration Zone Awabel Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 06, 2026)
- Posted at: 2026-10-06T09:37:53.000Z
- Source: Qelal Tenders