Stationery

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት እቃዎችን እና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት፣ ለማሰራት እና ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የመጀመ ሪያ ዙር የጨረታ ማስታ ወቂ ያ የጨረታ ቁጥር 001/2019 በ ጀት ዓመት

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥራቱን የጠበቀ እቃ ለመግዛት ስለፈለግን

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ እቃዎች፡ የመኪና እቃዎች የጽዳት እቃዎች፤ የጓሮ አትክልት፡ ዘር፡ የደንብ ልብሶች የደንብ ልብስ ስፌት፤ ህትመት፤ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ጥገና፤ ዲኮር፡ ድንኳን ኪራይ፤ ጫኝና አውራጅ፤ የህዝብ ትራንስፖርት እና የደረቅ ጭነት አገልግሎት፡ የምግብ ግብዓቶች፡ ዶሮዎችናየዶሮመኖ ወዘተ የመሳሰሉት
  • መስተንግዶ (የካፌአገልግሎት) ለምትወዳደሩ፡ በማህበር የተደራጁ (በስራ እድል ) የተደራጁ መረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  • የቢሮ መገልገያ እቃዎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎችን እና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ፡ ለማሰራት እና ለመሸጥ ይፈልጋል።

 በዚህ መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።

1. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እና የሚያስገቡት እቃ ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው

2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው

3. ተጫራቾች ናሙና አቅራቢው በኮሚቴ ከተመረጠላቸው በኋላ ዓይነቱን የመቀየር፣ የማጭበርበር ወይም ጥራት የመቀነስ ሁኔታ ቢታይ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑንና በተጨማሪም በህግ የሚያስቀጣቸው እንደሆነ መታወቅ አለበት።

4. ለወጣው ጨረታ በዘርፍ የተሰማሩ እና ለሚወዳደሩበት ሎት አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅ ባቸው መንግስት ከፈቀደላቸው ዘርፎች ውጪያሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ሠነዱን ሲያስገቡ ኦርጅናልና ኮፒው በማህተም የተደገፈና የባለቤትነት ሁኔታ ግልጽ የሚያደርግ ሌላ ህጋዊ ተጨማሪ ማስረጃ ካለ በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በብር መጠን በየሎቱ እንደሚከተለዉ በየሎቱ ማስያዝ አለባቸው

6.1 ሎት1/እስቴሽነሪ የብር መጠን 20,000 (ሀያሺህ ብር)

6.2 ሎት2/የጽዳት እቃ የብር መጠን20,000 (ሀያሺህ ብር)

6.3 ሎት3/የደንብ ልብስ የብር መጠን25,000 (ሀያ አምስት ሺህ ብር)

6.4 ሎት4/ የቋሚእቃ የብር መጠን 10,000(አስርሺህ ብር)

6.5 ሎት5/የጓሮ አትክልት ዘር የብር መጠን 5,000 (አምስት ሺህ ብር)

6.6 ሎት6/የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የብር መጠን 10,000 (አስር ሺህ ብር)

6.7 ሎት7/ህትመት ስራ የብር መጠን5,000 (አምስት ሺህ ብር)

6.8 ሎት8/መስተንግዶ የብር መጠን20,000 (ሀያ ሺህ ብር)

6.9 ሎት9/የህዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የብር መጠን 8,000 (ስምንት ሺህ ብር)

6.10 ሎት10/የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎትየብርመጠን 5,000 (አምስት ሺህ ብር)

6.11 ሎት11/ፈርኒቸር ጥገና አገልግሎትየብር መጠን 1,000 (አንድ ሺህ ብር)

6.12 ሎት12/የዲኮርና ድንኳን የማቅረብ አገልግሎት የብር መጠን 5,000 (አምስት ሺህ ብር)

6.13 ሎት13/ጫኝና አውራጅ አገልግሎት የሚሰጥ የብር መጠን 4,000 (አራት ሺህ ብር)

6.14 ሎት 14/ የምግብ ግብዓቶች ዘይት፡ዱቄትወዘተ የብር መጠን 5,000(አምስት ሺህ ብር)

6.15 ሎት 15/ እንስሳቶችና የእነስሳት ምግቦች10,000(አስርሺህብር)

6.16 የሚሸጡ ንብረቶች የብር መጠን 4,000 (አራት ሺህ ብር)

በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለበት በአስረኛው ቀን 11፡30 ላይ ታሸጎ ጨረታው በተጠናቀቀ ማግስት ወይም በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

7. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የእቃና የአገልግሎትግዥ እንደማይሳተፋና ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል።

8. ለጨረታው ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 20%ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ12 ፋይናንስ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ አለበት።

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ያልተሟላ ከሆነ ከጨረታውውጪ እንደሚሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

13. ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በቴሌብር በመክፈል ከወረዳ2 ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲሱ ህንፃ ከ6ኛፎቅ ላይ ቀርበው መግዛት ይችላሉ ነገርግን ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ተጫራቾች የሚያጽፉት ደብዳቤ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ላይ እሴት የሚጨምሩበት መሆኑን ተገልፆ መጻፍ አለበት ካልሆነ ግን የማናወዳድር መሆኑንን እንገልጻለን።

14. ማንኛውም ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በቀረበው የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግም ይሁን ማሻሻያ ማቅረብ ወይም ከጨረታው እራሱን ማግለል አይችልም፣ይህ ሆኖ ከተገኘ በጨረታው ህግ መሰረት የሚቀጣ መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል።

15. ጨረታውን ሲያስገቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

16. የሚሸጡ ንብረቶች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በቴሌ ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 09-471 57863 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ የወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ላፍቶ ታ ክሲ ማዞ ሪያው ፖሊ ስ ጣቢ ያው ጋር እንገኛለን።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12  አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-10-15
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30
  • Bid opening: 2026-10-16 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በተጠናቀቀ ማግስት ወይም በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Oct 06, 2026)
  • Posted at: 2026-10-06T11:23:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders