Spare Parts and Car Decoration Materials
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ/ጽ/ቤት የግን/አስ/ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ የመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ/ጽ/ቤት የግን/አስ/ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ላሉ የመንግስት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል
- ሎት አንድ የመኪና መለዋወጫ
- ሎት ሁለት የመኪና ጎማ ፤ ባትሪ
- ሎት ሶስት ሶስት የመኪና ዘይትና ቅባት
- ሎት አራት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ
ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሱ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው
- ከታክስ ባለስልጣን ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ግዡ ከ500, 000/አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መሂ/1 ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ መ/ሂ/1 ማስያዝ የሚችል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል ወይም በገንዘብ ጽቤት ብቻ ይሆናል። አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ29/01/2019 ዓ/ም እስከ 08/02/2019 ዓ/ም በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላቹሁ።
- የጨረታ ሳጥኑን በ09/2/2019 ዓ/ም 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ካላንደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን 9፡00 ታሽጎ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊው ሎት እንድን ጎንደር ከተማ ማቅረብ የሚችል እና በተጠየቀ በአምስት ተከታታይ ቀናት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ የሚችል። ሌሎቹን ሎቶችን ግን በየዳ ወረዳ ድል-ይብዛ ከተማ በአራቱ ንብረት መጋዝን ማቅረብ የሚችል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 35 22 28 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-19
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-10-19 15:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Beyeda Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 09, 2026)
- Posted at: 2026-10-09T08:02:15.000Z
- Source: Qelal Tenders