Disposal Sale
ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አሥራ ሰባት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሸያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001
ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አሥራ ሰባት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይልጋል።
የጨረታው መመሪያዎች፡-
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ በመግዛት በባንክ አካውንት ቁጥር በዳሸን ባንክ 0122001545005 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000317295484 የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ገቢ አድርገው ደረሰኙን በማቅረብ ሣር ቤት አዳምስ ፋቢሎን በሚወስደው ኪያብ ሕንፃ 5ኛ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተሽከርካሪዎቹን ሰሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚፈልጉትን የመኪና አይነትና የሠሌዳ ቁጥር ከሚዝዙበት ዋጋ ጋር በመጥቀስ እና ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የሚፈልጉትን መኪና መነሻ ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ በማያያዝ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሊገዙ የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ በማስገባት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ማግስት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በዋናው መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው ነገር ግን አንድ ተጫራች ለእያንዳንዱ መኪና የጨረታ ማስከበሪያ የተጠየቀውን ሲፒኦ በማቅረብ ከአንድ መኪና በላይ መጫረት ይችላል።
- ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ7፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
- በጨረታው ለሚሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል። ለአሸናፊዎች ግን ከግዢው ከፍያ ላይ ታሳቢ ይሆናል።
- ድርጅቱ መኪናዎቹን ለመሸጥ የሚያስፈልጉ ክሊራንስ በራሱ ወጪ ከሚመለከተው መንግስት መ/ቤት ያቀርባል።
- የጨረታ አሸናፊዎች የስም ማዘዋወሪያና በሽያጩ ምክንያት የሚጣለውን ማናቸውንም ግብር፣ ቀረጥና የተሽከርካሪው የሽያጭ ግምት ክፍያ እንዲሁም ሎሚገዟቸው መኪናዎች ማናቸውንም ተዛማጅ አገልግሎቶች ወጪ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ይሸፍናሉ።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን የመኪና ዋጋ ከፍለው በሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ መኪናዎቹን ማንሳት አለባቸው" ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙት ገንዘብ ሲፒኦ/ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው አሸናፊነት ይሰረዛሉ።
- የጨረታ አሸናፊዎች በሦስት ወራት ውስጥ የባለቤትነት ስም ዝውውር መጨረስ አለባቸው።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
ለተጨማሪ መረጃ፡-
አድራሻችን፡- ሣር ቤት አዳምስ ፋቢሎን ዝቅ ብሎ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ
በኪያብ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ወይም
በስልክ ቁጥር።- 011 372 26 38 ወይም 011 371 79 44 ወይም 011 372 26 40
ኢ-ሜይል Inforainbowethiopiqours.com አዲስ አበባ
ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ
አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-10-28
- Bid closing time: 13:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-28 13:00
- Bid opening (note): ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ7፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Rainbow Exclusive Car Rental and Tour Service PLC
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 11, 2026)
- Posted at: 2026-10-12T10:46:08.000Z
- Source: Qelal Tenders