Other Sales
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር 14/2019
በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም www.auction.et (አፕሊኬሽን) ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤
በመሆኑም
1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ
4. ከሀሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5, በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት |
የእቃ ግልፅ |
እስከ 10/02/2019 |
11/02/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
7. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ፡፡
8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት፦ በስልክ ቁጥር 0905 115 511
አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡- 0114 708 503
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-21
- Bid closing time: 09:45
- Bid opening: 2026-10-21 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 12, 2026)
- Posted at: 2026-10-13T09:30:05.000Z
- Source: Qelal Tenders