Fuel and Lubricants
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-06/2019
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት /በጥቅል/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጀዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የናፍታ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 04/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 14/-02-/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሽግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ04/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 14/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዘይትና ቅባቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በ14/-02-/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155/ 058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረ ሆን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ባህርዳር
ፖሳቁ 382
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-10-24
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-24 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Rural Roads Construction Authority
- Bid bond: የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Oct 14, 2026)
- Posted at: 2026-10-14T08:10:39.000Z
- Source: Qelal Tenders