Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መሥሪያ ቤቶች የሆኑ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን፣ ሞተር ሳይክሎችን፣ ጄነሬተሮችን እና ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 05/2019
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎችና ጄነረተሮች እና ማሸነሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 01/03/2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
1, የኤጀንሲዉ አድራሻ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጲያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት/ ጫፌ አናኒ ህንጻ ከሚገኘዉው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከየመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 rd floor) ቢሮ ቁጥር -02 መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሕዳር 01/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30— 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 02/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጫረታው ሕዳር 02/03/2019 ዓ.ም ከጥዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መናሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ /የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
CPO ለማሰራት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111 834 0535
ፊንፊኔ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Tender details
- Deadline: 2026-11-11
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-11-11 11:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Public Procurement and Property Disposal Agency
- Buyer address: Sarbet, Kera road, In front of Pushkin square on Bethlehem Building 3rd floor
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Oct 15, 2026)
- Posted at: 2026-10-15T08:25:36.000Z
- Source: Qelal Tenders