Equipment and Accessories

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 12/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ስካን በማድረግ ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርቦታል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው ጊዜ መሰረት በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ኦንላይን በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
  3. ያገለገለ ተሸከርካሪ/ሞተርሳይክል) ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥምየተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.PO በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. ቅ/ጽ/ቤቱ ቢሮ ወይም ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በአካል በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው ቀን ጥቅምት 08 ቀን 2019 ጀምሮ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ስለሆነም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ንሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታዉ ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ዉጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ዉድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (3) ቀናት የሚመለስላቸው ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በተለጠፈው ፎቶ ብቻ ተመልክተው ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
  12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55 11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር፡- 046-212-5396/ 046- 212-6595 ይደውሉ
የቴሌግራም ግሩፕ - https://t.me/hawassaawegaged  (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) ይጠቀሙ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-23 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Oct 18, 2026)
  • Posted at: 2026-10-19T09:20:57.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders