Disposal Sale
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጉምሩክ ቀረጥ የተከፈለባቸው የተለያዩ ሞዴል ያላቸው 15 /አስራ አምስት/ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጉምሩክ ቀረጥ የተከፈለባቸው የተለያዩ ሞዴል ያላቸው
- 15 አስራ አምስት/ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- የተሸከርካሪዎቹን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታ ሰዓት ድረስ ማየት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ተሽከርካሪዎቹን ከተ.እ.ታ በፊት የሚገዛበትን ዋጋ 10% ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ ማድረግ ወይም በሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ጨረታው ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 10:15
- Bid opening: 2026-11-19 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
- Buyer TIN: 0000028921
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T07:55:51.000Z
- Buyer website: https://www.aaae.gov.et/en/
- Source: Qelal Tenders