Disposal Sale
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ሲሆን/ ድርጅቱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና በጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ የሚገኝ ሲሆን / ድርጅቱ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ አዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ የመንገድ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎችና ሜካኒኮች ማሰልጠኛ ፊትለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ መግዛትና ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ::
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጂናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር እባሪ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው:: የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል:: ተጫራቾች ስለ ንብረት አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ የተቀመጠውን የተጫራቾች መመሪያ ማንበብ ይኖርባቸዋል:: ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 393393 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ:: ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት
(CCRDA)
Tender details
- Deadline: 2026-10-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-10-29 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Consortium of Christian Relief and Development Association (CCRDA)
- Buyer's registered address: Akaki kality Sub City, Debreziet Road In front of Drivers and Mechanics Training Centre
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Reporter (Oct 18, 2026)
- Posted at: 2026-10-20T09:38:47.000Z
- Source: Qelal Tenders