Other Sales

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ የተለያዩ ንብረቶችን በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር -11/2019 ዓ.ም

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ WHEEL LOODER፣ BAJAJ፣ ተሽከርካሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጫማ፣ አልባሳት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቧንቧ ብረት እና ምግብ ነክ በግልፅ እንዲሁም አጎበር፣ የገና አባት ልብስ /santasuit/ እና ኮስሞቲክስ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹም፡-

1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም ዕድሜው ከ-18-ዓመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።

2) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።

3) በጨረታ የሚሸጠው ዕቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

4) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።

5) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

6) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።

7) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።

8) ተጫራቾች ለዕቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።

9) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ ዕቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።

10) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ ዕቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እንዲሁም የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 / መቶ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

11) መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 0693 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-28 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T09:27:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders