Other Sales

ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣የተወረሱ እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ኮስሞቲክስ እና የእጅ ሰዓት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ጅማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ኮስሞቲክስ እና የእጅ ሰዓት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ ከጥቅምት 13/2019 ዓ.ም 2፡00 ሰዓት እስከ ጥቅምት 18/209 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ድረስ በኦንላይን ኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም፡-

1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡ ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀናና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ክሊራንስ) ፎቶ በማንሳት ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርበታል። ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ። ከኦላይን የጨረታ ሠነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ተጫራቹ 200,000(ሁለት መቶ ሺህ) ብር በጅማ/ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ ማስያዝ ይኖርበታል።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን ማስታወቂያ ከወጣበት ከቀን

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

1

ጅማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

ሐራጅ

13/02/2019 እስከ 17/02/2019 ዓ.ም

ጥቅምት 18/2019 4:00 ሰዓት ላይ ኮስሞቲክስ የሚዘጋ ሲሆን የእጅ ሰዓት ደግሞ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡20 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-211-6287 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ 09-05-11-55-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-28
  • Bid closing time: 10:20
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-10-28 10:20
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ)
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Oct 23, 2026)
  • Posted at: 2026-10-23T09:31:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders