Equipment and Accessories
አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 51/2019
አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሱትን ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ዕቃውን መግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከ 13/2/2019 ዓ.ም. ጀምሮ የማይመለስ ቫትን ጨምሮ ብር 115.00 / አንድ መቶ አስራ አምስት / በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን
በጨረታው ለመወዳደር መሟላት የሚገባቸው ማስረጃዎች
1. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ለእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት ከቫት በፊት እና ከቫት ጋር መሆኑን በግልፅ በኤንቨሎኘ አሽጐ ማቅረብ ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ይህ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አቅርቦት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡትን ዋጋ 5% በአሰር ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ኩባንያ ስም በተዘጋጀ ርPዐ በተናጠል በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
5. ጨረታው 20/2/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ 20/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት አካባቢን በማይበክል እና በሰዎችም ላይ የጤና እክል በማያስከትል ሁኔታ ጥቅም ላይ ለማዋል ዋስትን በጽሁፍ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
7. አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ ላሸነፉት ንብረት በ5 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል በ15 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ነው ዕቃውን ማንሳት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ባይሆን ግን ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
8. የጨረታ ሰነድ በሚያስገቡበት ወቅት ቅድመ ሁኔታ ጽፎ ማቅረብ ከውድድር እንዲሰረዝ ያደርጋል።
9. ኩባንያው የተሻለ መንገድ/አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡
ሁሉም ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች የሚሸጡት ባሉበት ቦታና ሁኔታ መሆኑን እንገልፃለን።
መረጃ ከፈለጉ ፡ 0116-39-20-64 መደወል ይችላሉ የዋና መ/ቤት አድራሻ ከቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል አጠገብ ከሚገኘው ዲኤች ገዳ ጀርባ።
|
የዕቃው ዓይነት
|
መለኪያ |
መጠን
|
ነጠላ ዋጋ
|
ጠቅላላ ዋጋ
|
የሚገኝበት ቦታ
|
||
|
የሬንጅ በርሜል ባለበት |
በቁጥር
|
1,500
|
|
|
|
|
ቡልቡላ አስፋልት ፕላንት
|
|
የዘይት በርሜል ባለበት |
በርሜል
|
20 |
|
|
|
|
ቃሊቲ ማእከላዊ ጋራጅ |
|
የተለያየ ዓይነት ያገለገለ የመኪና ጎማ ባለበት |
በርሜል |
18 |
|
|
|
|
ቃሊቲ ማእከላዊ ጋራጅ 70 Amper=8 እና 150 Amper= 10 |
|
የተለያየ ዓይነት ያገለገለ የመኪና ጎማ ባለበት
|
በቁጥር |
78 |
|
|
|
|
ቡልቡላ አስፋልት ፕላንት=23፤ ዋና ቢሮ =17 ክሬሸር ቁጥር-1=38 |
|
የተለያየ ዓይነት የፕሪንተር ቶነር ባለበት |
በቁጥር |
110 |
|
|
|
|
ክሬሸር ቁጥር-1 |
|
የተቆራረጠ ብረትና ቆርቆሮባለበት
|
ኪሎግራም
|
1,700 |
|
|
|
|
ክሬሸር ቁጥር-1 =200 እና ባቺንግ ፕላንት=1500፤ |
|
የተለያየ ዓይነት ሳክሽን ፤ የክሬሽር ኮንቨየር ቤልት እና የፕላስቲክ ውጤቶች ባለበት |
ኪሎግራም
|
200 |
|
|
|
|
ክሬሸር ቁጥር-1
|
|
የሲምንቶ ወረቀት ባለበት
|
በቁጥር
|
6,600 |
|
|
|
|
ባቺንግ ፕላንት=1000፤ ክሬሸር ቁጥር- 2=5000 እና ክሬሸር ቁጥር-1-600 |
|
ድምር |
|
|
|
|
|
||
|
ቫት 15 % |
|
|
|
|
|
||
|
ጠቅላላ ድምር |
|
|
|
|
|
||
Tender details
- Deadline: 2026-10-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-10-30 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Aser Construction P.L.C.
- Buyer TIN: 0005095896
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 115.00 /አንድ መቶ አስራ አምስት/
- Published on: Qelal Tenders (Oct 24, 2026)
- Posted at: 2026-10-24T07:10:02.000Z
- Source: Qelal Tenders