Wood and Wood Working

ያገለገለ የእንጨት ማሽኖች (የእንጨት ውጤት መስሪያ ማሽኖች) ግራይንደር፣ ድሪል፣ ቻርጅ፣ ድሪል መሰንጠቂያ፣ መቁረጫ፣ ማለስለሻ እና ሹተር እና የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አዱኛ የሺጌታ እና የፍ ባለዕዳ አቶ ፍቅሩ ቢረጋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/181964 በ16/06/2015ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/196513 በ30/05/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1ኛ በፉሪ ከ ከተማ ሙዳ ፉሪ ወረዳ ቀበሌ 04 የቤት ቁጥር -- ውስጥ የሚገኙ ያገለገለ የእንጨት ማሽኖች (የእንጨት ውጤት መስሪያ ማሽኖች) ግራይንደር፣ ድሪል፣ ቻርጅ፣ ድሪል መሰንጠቂያ፣ መቁረጫ፣ ማለስለሻ እና ሹተር የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 122,500 ( አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡ዐዐ ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ 2ኛ በኮ/ቀ/ከ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ 2-38596 አ/አ የሆነ ተሸከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,100,000 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ) ሆኖ የትራዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 8 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ መሉ ገንዘቡን በ15ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-17 14:30
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Oct 24, 2026)
  • Posted at: 2026-10-24T07:41:34.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders