Spare Parts and Car Decoration Materials

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎ/ዞ ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በማሕቀፍ የግዥ ስልት ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ  ማስታወቂያ

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎ/ዞ ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-

  • ሎት 1. የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃ
  •  ሎት 2 የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ
  • ሎት3. የተሽከርካሪ ዲኮር
  •  ሎት4.የተሽከርካሪ ዘይቶች እና ቅባቶች
  •  ሎት 5. የፎቶ ኮፒ አገልግሎት
  • ሎት6. ህትመት
  •  ሎት7. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ መለዋወጫ እቃዎች
  •  ሎት8. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ በኮንትራት ውል የሚያዝ ሲሆን

 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በማሕቀፍ የግዥ ስልት፡- ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል። የጨረታ መለያ ቁጥር 02 በዚህም፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /Aፐ/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. በተጫራቾች የሚቀርበው የመዋዳደሪያ ዋጋ ለእቃና አገልግሎት ለ45 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፤
  6. የሚገዙ እቃዎችን/አገልግሎቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር በመ/ቤቱ መሂ-1 በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ
    • ሎት 1. የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ)
    • ሎት 2. የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ ብር 40,000(አርባ ሺህ)
    • ሎት3. የተሽከርካሪ ዲኮር ብር 10,000(አስር ሺህ)
    • ሎት4 የተሽከርካሪ ዘይቶች እና ቅባቶች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ)
    • ሎት5.የፎቶ ኮፒ አገልግሎት ብር 3,000(ሶስት ሺህ)
    • ሎት.6 ህትመት ብር 3,000 (ሶስት ሺህ)
    • ሎት7. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ መለዋወጫ እቃዎች ብር 5,000(አምስት ሺህ)
    • ሎት8 የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ ብር 3,000(ሶስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእቃና አገልግሎት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ሞልቶ እስከ 4፡00 ሰዓት  ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መምሪያው ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን እንዲታወቅ፤ ሆኖም የጨረታው መከፈቻ ቀን የበዓላት ቀን ወይም የካላንደር ዝግ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  10. የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ፣ኮሬክሽን ፍሉድ መጠቀም ወይም መፋቅ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።
  11. ተጫራቾች መ/ቤቱ ካዘጋጀው የስራ ዝርዝር ስፔስፍኬሽን ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያደርጋል።
  12. በሎት3፤ ሎት5፤ሎት6 እና ሎት8 በተመለከተ በደ/ማርቆስ ከተማ ላይ ቅርንጫፍ ከፍቶ አገልግሎቱን መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
  13. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
  14. በሎት4 የተጠቀሰው የተሽከርካሪ ዘይት እና ቅባት እቃ የማሕቀፍ የግዥ ስለትን አይከተልም።
  15. አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ሲሆን በከፊል የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሙላት እንዲሁም ጠቅላላ ድምር ሞልቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል።
  16. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ወይም ውል የያዙባቸውን እቃዎችና አገልግሎት በምስ /ጎ/ዞን መምሪያዎች ባሉ የፑል ንብረት ክፍሎች ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  17. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  18. ሙስና ላለመፈጸም ቃል የሚገባበትን ቅጽና ሌሎች በተጫራቾች ተሞልተው እንዲቀርቡ መደረግ አለበት።
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም።
  20. የተጫራቾችን መመሪያን(SBD) በሶፍት ኮፒ ከግዥና ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር- 01 ላይ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  21. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምስ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመቅረብ ምስ ጐጃም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ ግራውንድ ቢሮ ቁጥር- 01 ወይም በስልክ ቁጥር 058 777 16817 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የምስ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-06 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: East Gojam Zone FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T10:25:02.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders