Spare Parts and Car Decoration Materials

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የተያዙና የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 16/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፤ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም

1. በዕቃ ግልጽና ሀራጅ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ፎቶ በማንሳት(ስካን በማድረግ) ኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et ማያያዝ ይኖርበታል።

2. በጨረታው ላይ የዕቃው ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ወይም www.auction.et ላይ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMSSON ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ያሰሩትንም ሲፒኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

5. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተቁ 4 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰነ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን። ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው ወይም ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

የእቃ ሀራጅ

እስከ 23/02/2019

እስከ 24/2019 (ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ደቂቃ መሠረት ይካሄዳል።

2

የእቃ ግልፅ

እስከ 24/02/2019

ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል።

7. የጨረታ መክፈቻ ቦታ ሙሉ በሙሉ የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ወይም www.auction.et (በኦንላይን) የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደት በኦንላይን መከታተል ይችላሉ።

8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09 -05 -11 -55 -11

አድራሻ፡- ቦሌ አትላስ አውሮፓ ህብረት ዝቅ ብሎ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ

ቁጥር 301 (ኦክሽን ኢትዮጵያ)

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡- 011 -470 8503

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-04 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Oct 27, 2026)
  • Posted at: 2026-10-27T11:51:04.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders