Equipment and Accessories

ድጋሚ የወጣ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ ለገስ ወርቁ እና የፍ/ባለዕዳ ናሽናል ዕሴት ማኔጅመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/17760 በ30/07/2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ.20682 በ11/10/2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.20682 በ5/10/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አቢሲኒያ ሕንፃ ላይ የሚገኙ ፍ/ያረፈባቸው ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች እና ሌሎች ንብረቶች የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 635,199 (ስድስት መቶ ሠላሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.20682 በ05/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የመነሻ ዋጋ በገበያው ሁኔታ መሠረት የ50% ቅናሽ በማድረግ በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ 1/4ኛ ብር 158,799.75 (አንድ መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ከ75/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ኅዳር 21 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-30
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-11-30 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T07:31:40.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders