Other Sales
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች(መኪናዎች፣ ትራክተር ፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች(መኪናዎች፣ ትራክተር ፣ ተጎታች ጋሪዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-
- ሎት 1 መኪናዎች
- ሎት 2 ትራክተር
- ሎት 3 ተጎታች ጋሪዎች
- ሎት 4 ሞተር ሳይክሎች
- ሎት 5 ብስክሌቶች
1. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ እና ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡ ሎት 1 መኪና ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ፣ ሎት-2 ትራክተር ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ ፣ ሎት-3 ተጎታች ጋሪ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ ፣ ሎት-4 ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እና ሎት-5 ብስክሌቶች ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
7. ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሽከርካሪዎች የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ተሽከርካሪ/ዎች ውጪ መወዳደር አይቻልም፡፡
8.ተጫራቾች በተዘጋጀውየጨረታሰነድመሠረትከአንድ በላይተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር ፣ ተጎታች ጋሪዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች መጫረት ይችላሉ፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ሃያ አንድኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
10.ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር ፣ ተጎታች ጋሪዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።
11.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር ፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።
12. አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።
13. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-2337/236 ደውሎ መጠየቅ የሚቻልመሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ሃያ አንድኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ሃያ አንድኛው ቀን ከጧቱ 5፡00 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Hadiya Zone Finance Bureau
- Bid bond: 20%
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T09:08:08.000Z