Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ  ቁጥር 45/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ

  • የሞተር ሳይክል እና
  • የተሸከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፤
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • የመገናኛ መሳሪያዎች ኮስሞቲክስ እና
  • የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና
  • ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም 
  • ሌሎች ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች የግልጽ እና ሃራጅ ጨረታ ሰነድ በቴሌግራም አካውንት የሚላክላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት ዘወትር በስራ የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ሌሎች ከላይ የተገጹ 10 አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወክሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
  6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቅቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
  7.  ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፍ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 444 1415/ 046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 09:45
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቅቃ)
  • Bid opening: 2026-08-17 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው 4፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Moyale Customs Branch Office
  • Bid bond: በግልፅ ጨረታው 5% እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T07:32:12.000Z
← Back to all tenders